GET INVOLVED
Young Life የተመሰረተው ለአካለ መጠን የደረሱ ወጣቶችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለማስተዋወቅ እና እምነታቸውን ይዘው እንዲያድጉ ለመርዳት ነው። Young Life ይህን ተልዕኮውን በ50 የዩናይትድ ስቴትስ እና በመላው አለም በ90 ሀገራት በሚገኙ በ90 የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ለኮሌጅ ትምህርት በደረሱ ወጣቶች ዘንድ በንቃት ያካሂዳል።
ይህን አለም አቀፍ ተልዕኮ ለማስቀጠል Young Life እና የተለያዩ ተያያዥ አገልጋይ ድርጅቶቹ (Young Life) የርስዎን የግል መረጃ ሊሰበስቡ፣ ሊያቀናብሩ፣ ሊጠቀሙና ሊገልጹ ይችላሉ። የዚህ የግላዊነት መግለጫ አላማ ለርስዎ እንዴት Young Life የግል መረጃዎን ሊገልጽ እንደሚችል እና እንዴት የርስዎነ መብቶችና የግል መረጃዎን ለመጠበቅ ግደታዎቹን በጥንቃቄ እንደሚፈጽም በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ነው።
‹‹ Young Life››፣ ‹‹እኛ››፣ ‹‹የኛ›› የሚሉት ቃላት ጥቅም ላይ በሚውሉበት ጊዜ ቃላቱ Young Life - የቴክሳስ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅትን እና ተቀጽላና ተባባሪ ድርጅቶቹን ይወክላሉ። ‹‹የግል መረጃ›› በጠቅላላው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከእርስዎ ጋር የሚገናኙ ሁሉንም ዳታ ይገልጻል፣ ሆኖም ‹‹የግል መረጃ››፣ ‹‹የግል ዳታ›› ወይም ‹‹የግል መለያ መረጃ›› እና ሌሎች አገላለጾች በተፈጻሚ ህግ ላይ ተመስርቶ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ሲሆን በዚህ ጊዜ የእነዚህን ተፈጻሚ ህጎች ትርጉም ይይዛሉ።
ከጊዜ ወደ ጊዜ በዚህ የግላዊነት መግለጫ ላይ ማሻሻያ ልናደርግ የምንችል በመሆኑ መግለጫውን በየተወሰነ ወቅት እንዲመለከቱ፣ ከላይ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ማሻሻያ የተደረገበት›› ለሚለው ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ እናበረታታዎታለን። በአንዳንድ ሁኔታዎች Young Life ከእርስዎ ጋር ግንኙነት በማድረግ በተለይም በዚህ የግላዊነት መግለጫ ላይ የተደረጉ ለውጦችን ያሳውቅዎታል።
የሚሰበስባቸውን፣ የሚቀናብራቸውን፣ የሚጠቀማቸውን እና የሚገልጻውን የግል መረጃዎች በመያዝ ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተሞላበት አሰራር መከተል የ Young Life አጠቃላይ ፖሊሲ ነው። Young Life የግል ዳታ ጥበቃን ለማሳደግ እና የተፈጻሚ ህጎችና ደንቦች መከበርን ለማረጋገጥ በአጠቃላይ/አለም አቀፍ ተልዕኮው ላይ ተገቢ ፖሊሲዎችና አሰራሮችን ይከተላል። Young Life በተጨማሪም እንደ አጠቃላይ የግል ፕሮግራሙ አንድ ክፍል በእነዚህ ፖሊሲዎችና አሰራሮች ላይ ወቅታዊ ማሻሻያዎችን እና ጭማሪዎችን ለማድረግ በትጋት ይሰራል።
Young Life ተቀባይነት ካላቸው አለም አቀፍ የዳታ ግላዊነት መርሆች ጋር የሚጣሙ የዳታ ጥበቃ ፖሊሲዎችና አሰራሮችን የሚከተል አለም አቀፍ ድርጅት ነው። እነዚህ ፖሊሲዎች ለብሔራዊ የዳታ ግላዊነት ህጎች እና ከ Young Life ፖሊሲዎች ጋር ግጭት በሚፈጠርበት ወቅት ቅድሚያ ለሚሰጠው ለየትኛውም ብሔራዊ ህግ በተጨማሪነት ያገለግላሉ። በአውሮፓ አጠቃላይ የዳታ ጥበቃ ደንብ (GDPR) ከግንቦት 25/1218 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ሆኗል። GDPR እና/ወይም የEU የግላዊነት ህጎች በርስዎ ላይ ተፈጻሚነት የሚኖራቸው ከሆነ ይህ የግላዊነት መግለጫ ርስዎ እንዴት መብቶችዎን መጠቀም እንዳለብዎ ይገልጻል።
Young Life የሚከተሉትን አይነት የግል መረጃዎች ይሰበስባል፡
የግንኙነት መረጃ፡ የስልክ ቁጥርን፣ የመኖሪያ አድራሻን፣ የጽሁፍ መልዕክት አድራሻን፣ የኢሜይል አድራሻን፣ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የግል መረጃ ዝርዝሮችን ይይዛል።
የማንነት መረጃ፡ እርስዎ ማን እንደሆኑ፣ የት እንደሚኖሩ፣ እና ከYoung Life ፕሮግራሞችና ስራዎች ውስጥ በየትኞቹ ላይ መሳተፍ እንደሚፈልጉ የተመለከተ መረጃን ይይዛል።
የስራ ቅጥር መረጃ፡ የስራ ቅጥር ማመልከቻዎን ለማስተናገድ እና የስራ ቅጥር ሂደትዎን ለማጠናቅ የሚያስፈልግ መረጃን ይይዛል፤ ለምሳሌ፡ የስራ ቅጥር ታሪክ፣ ማመሳከሪያዎች፣ የወንጀል ክስ መዝገቦች፣ ልዩ የብቃት ደረጃዎች ወይም የሙያ ምርጫዎች
የፋይናንስ መረጃ፡ ለYoung Life ያደረጓቸውን ልገሳዎች፤ ከYoung Life የገዟቸውን አገልግሎቶች ወይም እቃዎች፣ ከ Young Life ጋር የፈጸሟቸውን ሌሎች የገንዘብ ግብይቶች የተመለከተ መረጃን ይይዛል።
የማንነት ዳታ፡ ስም፣ የትውልድ ቀን፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታን ይይዛል።
የግል እምነቶችን የተመለከተ መረጃ፡ የሀይማኖት መረጃን ይይዛል
የክፍያ መረጃ፡ የባንክ ሂሳብና የማስተላለፊያ ቁጥሮችን፣ የክሬዲት ካርድ/ዴቢት ካርድ ቁጥሮችን፣ የቼክ ቁጥር፣ ሌላ ተገቢ የፋይናንስ ዝርዝሮችን ይይዛል
ጥያቄዎችና ምርጫዎች፡ Young Life እንዴት ከእርስዎ ጋር ግንኙነት እንዲያደርግ እንደሚመርጡ፣ በየትኛውም የ Young Life የግል መረጃዎ ላይ የሚያደርጓቸውን ማሻሻያዎች የተመለከተ መረጃን ይይዛል
አስፈላጊ የጤና ዳታ፡ የህክምና መረጃዎን፣ የክትባቶች መዝገቦችን፣ የሀኪም ሪፖርቶችን እና የአሻራ መረጃን ጨምሮ እርስዎን በ Young Life ካምፕ ለመቀበል ወይም Young Life ጉዞ ወይም ዝግጅት ላይ ለማሳተፍ የሚያስፈልግ የጤና መረጃን ይይዛል
የደህንነት መረጃዎች፡ የመግቢያና የሚስጥር መግቢያ መረጃን ይይዛል
የጉዞ መረጃ፡ ከ Young Life ጋር ካደረጉት ጉዞ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን፣ የፓስፖርት መረጃን፣ የአመጋገብ ፍላጎቶችና ክልከላዎችን ይይዛል።
የበጎ ፍቃድ መረጃ፡ ምርጫዎችን፣ የወንጀል ክስ መዝገቦችን፣ ልዩ የብቃት ደረጃዎችን ጨምሮ የበጎ ፍቃደኝነት መረጃዎን ለማስናገድና የበጎ ፍቃደኝነት ቅበላ ሂደትዎን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልግ መረጃን ይይዛል።
የ Young Life መረጃ፡ የ Young Life ታሪክዎና ተሳትፎዎን የተመለከተ መረጃ
Young Life የሚሰጧቸውን የግል መረጃዎችዎን ጥያቄዎን በተሻለ ለማስተናገድ እና የ Young Lifeን ተልዕኮና ስራዎች ለማስቀጠል በሚያስችል መልኩ ይጠቀማል። እርስዎ በ Young Life ክለብ ወይም የካምፕ ፕሮግራም ይሳተፉም ወይም ጊዜዎን እና/ወይም ገንዘብዎን ለተልዕኳዊ አላማዎቻችን ያውሉም አያውሉም Young Life በጠቅላላው የግል መረጃዎን ከድርጅታዊ ተልዕኳችን ጋር ተያያዥ ህጋዊ ፍላጎቶቹን ለማሳካት ይጠቀምበታል። የግል መረጃዎን ለሌሎች አንሸጥም፣ በሊዝ ወይም ውሰት አሳልፈን አንሰጥም። Young Life የእርስዎን መረጃ የሚጠቀመው በተገቢ ህጋዊ መነሻዎች መሰረት እና በዚህ የግላዊነት መግለጫ ስር ለተገለጹት አላማዎች ብቻ ነው። ከዚህ በታች የቀረበው ሰንጠረዥ እንዴት የግል መረጃዎን እንደምንጠቀም፣ የምንጠቀማቸው አይነት መረጃዎችን እና የግል መረጃዎን ለመጠቀም የሚያስችሉ የህግ መነሻዎች ምሳሌዎችን ይዘረዝራል።
የግል መረጃዎን እንዴት እንደምንጠቀም
የምንጠቀማቸው አይነት መረጃዎች
ህጋዊ መነሻ
ምሳሌዎችና ማብራሪያዎች
Young Life በአካባቢዎ ስለሚያቀርባቸው የአገልግሎቱ ስራዎች በተመለከተ መረጃ ለመስጠት ከእርስዎ ጋር የሚደረግ ግንኙነት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ
ህጋዊ ፍላጎቶች
የ Young Life ሰራተኛ ወይም በጎ ፍቃደኛ እርስዎን በአካባቢዎ በሚገኝ የ Young Life ክለብ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ለመጋበዝ ስምዎን እና ስልክ ቁጥርዎን ወይም የኢሜይል አድራሻን ሊጠቀም ይችላል።
እርስዎ በYoung Life ካምፕ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ከተሳትፎው በኋላ በርስዎ ላይ ክትትል ለማድረግ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ አስፈላጊ የጤና ዳታ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ፣ የጉዞ መረጃ
ግንኙነት
በ Young Life ካምፕ ላይ ቢሳተፉ በህይወትዎ ውስጥ እጅግ አስደሳች ሳምንት ያሳልፋሉ ብለን ካሰብን የካምፕ ተሳትፎዎን ለማመቻቸት ከልጆችና ወላጆች የተወሰነ መረጃ መጠየቅ ሊያስፈልገን ይችላል።
የእርስዎን በ Young Life የመስክ ጉብኝት ላይ ተሳትፎ ለማመቻቸት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ አስፈላጊ የጤና ዳታ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ፣ የጉዞ መረጃ
ግንኙነት
Young Life አንዳዳድ አስደናቂ የአጭር ጊዜ የተልዕኮ ጉብኝቶች አሉት፤ ሆኖም ጉዞዎን በማስተባበር ላይ እርስዎን ለማገዝ እና ስለ ጉዞው በተመለከተ ጠቃሚ መረጃ ለእርስዎ ለመግለጽ ያስችለን ዘንድ የግል መረጃዎን ማግኘት ያስፈልገናል።
እርስዎ በ Young Life ኔትወርክ ላይ የግል መረጃዎን እንዲከፍቱ ለመርዳት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የደህንነት መረጃዎች
ግንኙነት እና ህጋዊ ፍላጎቶች
እርስዎ የሚሳተፉት ከዝግጅቶቻችን መካከል በአንዱ ላይ ይሁንም ወይም የ Young Life ታማኝ ለጋሽ ይሁኑም እርስዎ ከእኛ ጋር በቀላሉ ግንኙነት እንዲያደርጉ እንፈልጋለን። ስለሆነም እርስዎ ከYoung Life ጋር ያልዎትን ተሞክሮዎች የበለጠ እንዲያሳድጉ ለመርዳት የተለያዩ የኔትወርክ ውጤቶችን እንጠቀማለን።
ከ Young Life አገልግሎት ስራዎች ወይም ለ Young Life ልገሳ ለማድረግ ከሚያስችሉ እድሎች ጋር ተያያዥ ለሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ግንኙነት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ
ፍቃድ ወይም ህጋዊ ፍላጎቶች
ከዚህ በፊት ያላወቋቸውን የ Young Lifeን እድሎች ልናሳውቅዎት እንወዳለን፤ ሆኖም የማይፈልጓቸውን መልእክቶች ልንልክልዎ አንፈልግም። ቀደም ሲል እኛ ጋር ተሳትፎ አድርገው ከሆነ ከእርስዎ ጋር የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ግንኙነቶች ለማድረግ ህጋዊ ነን ብለን እናምናለን። ሆኖም እርስዎን መቆጣጠር ስለምንፈልግ እባክዎ ይህን አይነት መረጃ መቀበል እንደማይፈልጉ እንዲያሳውቁን እንፈልጋለን።
ከ Young Life ስራዎች ጋር በተያያዘ ለአካላዊ ግንኙነት (ምሳ፡ በፖስታ፣ የስልክ ጥሪዎች፣ ወዘተ)
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ
ህጋዊ ፍላጎቶች
ከጊዜ ወደ ጊዜ ለርስዎ ስለ Young Life ተሳትፎዎ ለማሳወቅ እና በህጻናት ላይ በምንሰራቸው ስራዎች ላይ ስለተደረጉ ወቅታዊ ማሻሻያዎች በተመለከተ ለማሳወቅ አሁንም የፖስታ አገልግሎት ልንንቀም እንችላለን
ለእርስዎ ስለ Young Life ዜናዎችና አዲስ መረጃዎች ለማሳወቅ የግብይት ላልሆኑ የኤሌክትሮኒክስ ግንኙነቶች
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ
ህጋዊ ፍላጎቶች
ሰራተኞቻችን በአብዛኛው በአገልግሎቶቻቸው ምን እየሰሩ እንደሚገኙ የተመለከቱ ታሪኮችና መረጃዎችን ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው ለጋሾች እና ወንድሞች ወቅታዊ መረጃዎችን ይሰጣሉ።
ለእርስዎ የ Young Life ሰራተኛ ወይም በጎ ፍቃደኛ ለመሆን እንዲያመለክቱ ለማስቻል
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የግል እምነቶችዎን የተመለከተ መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የደህንነት መረጃዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የግል አኗኗርዎ መረጃ
ግንኙነት
Young Life እጩ ሰራተኞች ወይም በጎ ፍቃደኞች በህጻናት ላይ የምንሰራቸው ስራዎችን ለመቀላቀል ብቁ መሆናቸውን በጥንቃቄ ለማረጋገጥ ይፈልጋል።
የእርስዎን ለ Young Life የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስራ ምዝገባ ለማመቻቸት እና ከዝግጅቱ በኋላ በርስዎ ላይ ክትትል ለማድረግ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ፣ የክፍያ መረጃ
ግንኙነት
የ Young Life ሰራተኛ ወይም በጎ ፍቃደኛ እርስዎ በአካባቢዎ ስለሚገው የ Young Life ስራ የበለጠ እንዲያውቁና ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል ለአካባቢዎ የጎልፍ ውድድር ወይም ግብዣ ላይ እንዲሳተፉ ሊጋብዝዎ ይችላል።
ለግንኙነት ተሳትፎ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ
ህጋዊ ፍላጎቶች
ከ Young Life ወይም መብቶችዎ ወይም የግል መረጃዎ ጋር በተያያዘ ለሚጠይቁን ጥያቄዎች በፍጥነት መልስ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ የግል መረጃዎን በሲስተማችን ላይ በተቻለ መጠን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ ተግተን እንሰራለን።
እንደ መንፈሳዊ መመሪያ ወይም የመጽሀፍ ቅዱስ ምክር ያሉ የአገልግሎቱን አገልግሎቶች ለማቅረብ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የግል እምነቶችዎን የተመለከተ መረጃ
ህጋዊ ፍላጎቶች
እግዚአብሔር እርስዎን እና ህጻናትን እንደሚወዳችሁ እናምናለን፤ እናም ሰራተኞቻችን እና በጎ ፍቃደኞቻችን ህጻናት ምን እያደረጉ እንደሆነና ለክርስቶስ ያላቸውን ፍቅር ሲገልጹ ለመስማት በህጻናት ህይወት ውስጥ መገኘት ይፈልጋሉ
እርስዎን የ Young Life ሰራተኛ አድርጎ ለመቅጠር
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የግል እምነቶችዎን የተመለከተ መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የደህንነት መረጃዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የስራ ቅጥር መረጃ
የውልና የህግ ግዴታዎች
የ Young Life ሰራተኛ ሆነው ለመስራት የስራ ቅጥርዎን ለማመቻቸት የሚያስችሉ የተወሰኑ መረጃዎችን መስጠት ይጠበቅብዎታል
እርስዎ ለ Young Life በበጎ ፍቃደኝነት የሚሰሩትን ስራ ለማመቻቸት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የግል እምነቶችዎን የተመለከተ መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የደህንነት መረጃዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የበጎ ፍቃደኝነት መረጃ
የውልና የህግ ግዴታዎች
የ Young Life በጎ ፍቃደኛ ሆነው ለመስራት የበጎ ፍቃደኝነት ስራዎን ለማመቻቸት የሚያስችሉ የተወሰኑ መረጃዎችን መስጠት ይጠበቅብዎታል
የእርስዎን ልገሳዎች ለመቀበል
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ
የውልና የህግ ግዴታዎች
ለ Young Life ልገሳ በሚሰጡበት ወቅት ልገሳዎን ለመሙላትና ተገቢ መዝገቦችን ለመያዝ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ እንጠይቅዎታለን።
ለህግ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታዎች
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ፣ የስራ ቅጥር መረጃ፣ የበጎ ፍቃደኝነት መረጃ
የህግ ግዴታዎች
Young Life የተወሰኑ የመንግስት ሪፖርት የማቅረብ ግዴታዎች ያሉበት ሲሆን ይህ ሪፖርት ማቅረብ የግል መረጃዎን የሚይዝ ሊሆን ይችላል ሆኖም ይህ Young Life በህግ መስጠት እስከሚገደድበት መረጃ ልክ ብቻ የተገደበ ነው።
የ Young Lifeን እቃዎችና አገልግሎቶች ለማቅረብ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የክፍያ መረጃ፣ የ Young Life መረጃ
ግንኙነት
ከኦንላይን ስቶራችን ቲሸርቶች ወይም ኩባያ ለመግዛት ሊፈልጉ፣ ወይም ለጎልፍ ውድድር ለመመዝገብ ሊፈልጉ ይችላሉ።
ስለ Young Life አገልግሎት ስራዎች፣ እቃዎችና አገልግሎቶች በተመለከተ የእርስዎን ግብረ መልስ ለመጠየቅ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የደህንነት መረጃዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የ Young Life መረጃ
የህግ ፍላጎቶች
ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማምጣት ያስችለን ዘንድ በዝግጅታችን ላይ ግብረ መልስ እንዲሰጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።
ለጥያቄዎችዎ መልስ ለመስጠት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የደህንነት መረጃዎች፣ የማንነት መረጃ
የህግ ግዴታዎች
ለየትኛውም ለ Young Life ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ የግል መረጃዎን እንጠቀማለን።
ለቅሬታዎችዎ መልስ ለመስጠት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ
የህግ ግዴታዎች
ለየትኛውም በYoung Life ለሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና ለየትኛው መብቶችዎን እና የግል መረጃዎን ለተመለከቱ ጉዳዮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ የግል መረጃዎን እንጠቀማለን።
የህጻናት ህጎችና ደንቦችን ለማሟላት
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ የስራ ቅጥር መረጃ፣ የበጎ ፍቃደኝነት መረጃ
የህግ ግዴታዎች
Young Life የህጻናትን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ ለማስጠበቅ እንደያዝነው ቁርጠኝነት አንድ ክፍል በየተወሰነ ወቅት የወንጀል የኋላ ታሪክ ማጣሪያዎችን እና የአሽከርካሪነት መጠይቆችን ያካሂዳል።
ፍላጎቱ ያላቸው የ Young Life ወንድሞችን በቀጣይ የ Young Life አገልግሎት ላይ ተሳታፊ ለማድረግ
የማንነት ዳታ፣ የግንኙነት መረጃ፣ ጥያቄዎችና ምርጫዎች፣ የማንነት መረጃ፣ የ Young Life መረጃዎ
ህጋዊ ፍላጎቶች
Young Life ከ Young Life-Alumni እና ወንድሞች ጋር በትጋት የሚገናኝበት አጠቃላይ የአገልግሎቱ ኢኒሺየቲቭ አለው። የ Alumni እና ወንድሞች ድረገጽና ፕሮግራም እርስዎን በ Young Life ውስጥ ተሳትፎና እንክብካቤ ከሚያደርጉ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዲገናኙ ያስችሉዎታል። የ Alumni እና ወንድሞች ድረገጽ በተጨማሪም ግንኙነት ወይም የመረጃ ልውውጡን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ተማራጭ አማራጮችን ይሰጣል።
ስለ እርስዎ የተመለከተ የግል መረጃ በሚከተሉት መንገዶች እንሰበስባለን፡
Young Life በጠቅላላው የግል መረጃን ከድርጅቱ ውጭ ለማንኛውም ሰው አይገልጽም። ሆኖም Young Life አለም አቀፍ ድርጅት እንደመሆኑ ከላይ ለተገለጹት አላማዎች የግል መረጃዎን ለሚከተሉት ሊገልጽ ይችላል፡-
Young Life በቅርንጫፍ ድርጅቶቹ፣ ተቀጽላዎችና ተባባሪዎች አማካኝነት በአለም የተለያዩ ክፍሎች የሚንቀሳቀስ አለም አቀፍ ድርጅት ነው። ስለሆነም Young Life የርስዎን የግል መረጃ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ሊያስተላልፍ ይችላል። በአውሮፓ ኢኮኖሚ አካባቢ ወይም ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ግለሰቦች የግል መረጃቸውን ለአጠቃቀም ከአውሮፓ ኢኮኖሚ አካባቢ ወይም ዩናይትድ ኪንግደም ውጭ ሊያስተላልፍ እንደሚችል ማወቅ አለባቸው።
የትኛውም ከሀገር ሀገር የሚደረግ የግል መረጃ ማስተላለፍ ተገቢ ጥበቃዎችን በማድረግና ተፈጻሚ ህጎችን አክብሮ ይካሄዳል። Young Life እና የአውሮፓ ተቀጽላዎቹና ተባባሪዎቹ ከአውሮፓ ሀገራት እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ወደመሳሰሉ ሌሎች አገራት የሚደረግ የዳታ ማስተላለፍ የሚተዳደርባቸው መደበኛ የውል አንቀጾች አዘጋጅተዋል።
የሚኖሩት በአውሮፓ ኢኮኖሚ አካበቢ ወይም ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከሆነ ከግል መረጃዎችዎ ጋር የተያያዙ የተወሰኑ መብቶች አሉዎ። የትኛውም እነዚህን መብቶች መጠቀም ከፈለጉ እባክዎ ለ Young Life በ privacy@younglife.org የኢሜይል መልዕክት ይላኩ። ለጥያቄዎ በ30 ቀናት ውስጥ መልስ እንሰጣለን። ጥያቄዎን ለማስተናገድ ያስችለን ዘንድ የእርስዎን ማንነት ማጣራት ሊኖርብን ይችላል።
እነዚህ የአውሮፓውያን መብቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡
የሰበሰብነውን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅና ለማረጋገጥ Young Life ያልተፈቀደ አጠቃቀምን መከላከያና የዳታ ትክክለኛነትን ማስጠበቂያ ተገቢ አካላዊ፣ የኤሌክትሮኒክስና አስተዳደራዊ ሥነ ሥርአቶችን ተግባራዊ አድርጓል። ጥንቃቄ የሚፈልጉ የባንክ ስርጭቶች ዳታ ወይም የክሬዲት ካርድ መረጃ የሚይዝ ዳታን ደህንነት ለመጠበቅ የኢንተርኔት ኢንክሪፕሽን ሶፍትዌር፣ ሰኪዩር ሶኬት ሎከር (SSL) ጥቅም ላይ ይውላሉ። በማውጫ ዊንዶዎ ላይ ከታች የሚገኘው የፓድሎክ ምልክት ወይም በዊንዶው ዙሪያ የሚገኘው ሰማያዊ መስመር የድረገጹ ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያሳያል። አንዳንድ ጊዜ የእርስዎን ግላዊነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚስጥር መግቢያ ጥበቃ ጥቅም ላይ ይውላል። Young Life አሁን ያሉትን የደህንነት ሥነ ሥርአቶች መጠቀሙን እና እንደ አስፈላጊነቱ በፖሊሲዎቻችን እና በዚህ የግላዊነት መግለጫ ላየይ የገለጽናቸው ቃል ኪዳኖቻችንን ለማሟላት የሚያስችል መደበኛ አያያዝን ለማሳካት አዳዲስ የደህንነት ፕሮቶኮሎችን ስራ ላይ ልናውል እንችላለን።
Young Life በተጨማሪም ለየትኛውም የዳታ ጥሰት ተገቢ ምላሽ ከመስጠት በተጨማሪ በተፈጻሚ ህግ በሚጠየቀው መሰረት ወቅታቸውን የጠበቁ ማስታወቂያዎችን የሚይዝ የዳታ ጥሰት ፕረቶኮል አሰራር እንጠቀማለን።
የ Young Life ድረገጾች እርስዎን ለማወቅ ጠቃሚ መልእክቨቶችን ሊጠቀሙና ድረገጻችንን በሚጎበኙበት በእያንዳንዱ ጊዜ የተጠቃሚ ስምዎን እና የሚስጥር መግቢያዎን ድጋሚ ማስገባት ሳያስፈልግዎ ወዲያውኑ እንዲገቡ ሊፈቅዱልዎ ይችላሉ። ጠቃሚ መልእክቶች የሚያዙ ቢሆንም እንደ የተጠቃሚ ስምዎን፣ የሚስጥር መግቢያዎ ወይም የኢሜይል አድራሻዎን የመሳሰሉ የትኛውንም የግል መለያ መረጃዎች ሴቭ አያደርጉም። በማውጫዎ ላይ ጠቃሚ መልዕክቶች እንዳይሰሩ ከተደረrጉ አሁንም የ Young Life ድረገጽን መጠቀም የሚችሉ ቢሆንም በሚገቡበት በእያንዳንዱ ጊዜ የሚስጥር መግቢያዎን ማስገባት ይጠበቅብዎታል።
ባጠቃላይ የ Young Life ድረገጾች ድርጅቱን በተመለከተ ለወላጆችና ህጻናት የመረጃ መስጫ ድረገጾች ናቸው። ህጻናትና ወላጆች Young Life ን የሚያውቁበት፣ የራሳቸውን የ Young Life ክለብ እና ሌሎች የ Young Lifeን ስራዎች የሚያገኙበት ምቹ፣ አዝናኝ ሁኔታ የመፍጠር ሀሳብ አለን። የ Young Life ያልሆኑ ድረገጾች በ Young Life ዝግጅቶች ወይም ስራዎች ላይ መሳተፍን ለማመቻቸት የግል መረጃ የግድ ከህጻናት እና/ወይም ወላጆች መወሰድ ካልኖረበት በስቸተቀር የግል መረጃን በሚታወቅ መልኩ እድሜያቸው ከ13 አመት በታች ከሆኑ ህጻናት ይወስዳሉ።
ለህጻናት ግላዊነት የምንጠነቀቅ ከመሆኑም በተጨማሪ የህሉንም ህጻናት የግል መረጃዎች ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን። አንድን ህጻን ለልዩ ስራ ተሳትፎ ከሚያስፈልገው ውጭ የትኛውንም የግል መረጃውን እንዲሰጠን የማንጠይቅ ከመሀሞኑም በተጨማሪ ለአንድ ህጻን ተሳትፎ በአንድ ተግባር ላይ ለመሳተፍ የግድ ተጨማሪ የግል መረጃ መስቸጠትን በፍጹም በቅድመ ሁኔታነት አናስቀምጥም። ሁሉም የምንሰበስባቸው የግል መረጃዎች ለተፈቀደላቸው የ Young Life ሰራተኞችና በጎ ፍቃደኞች፣ እና መረጃውን ከላይ ለተገለጹት አላማዎች ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ብቻ ይሰጣሉ። የመረጃውን ደህንነት፣ ሚስጥራዊነትና ሀቀኝነት ለመጠበቅ በትጋት እንሰራለን።
የህጻናት አገልጋይ እንደመሆናችን Young Life ለህጻናት ደህንነት በከፍተኛ ትጋት ይሰራል። ተፈጻሚ የግላዊነት ህጎች መከበርን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችና ሥነ ሥርአቶች ያሉን ከመሆኑም በተጨማሪ በተለይም ከወላጅ ማስቸታወቂያና ፍቃድ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ ተቀባይነት ያገኙ ተመራጭ አሰራሮችን ተግባራዊ እናደርጋለን። ወላጆች በየትኛውም ጊዜ ልጆቻቸውን በተመለከተ የተሰበሰበ መረጃ ከ Young Life ኔትወርኮችና የዳታ ቋቶች ላይ እንዲሰረዝ የመጠየቅ መብት አላቸው። Young Lifeን በ privacy@younglife.org ማነጋገር ይችላሉ።
ለግል፣ ቤተሰብ ወይም አባወራዎች የሚያገለግሉ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ከማግኘት ጋር በተያያዘ የግል መረጃቸውን የሚሰጡ የካሊፎርንያ ነዋሪዎች አንዴ የደንበኛውን መረጃ (ካለ) ለራሱ የቀጥተኛ ግብይት አጠቃቀም ለሌሎች የንግድ ድርጅቶች ከገለጽንበት የካላንደር አመት በኋላ መረጃውን ከእኛ ጠይቀው የማግኘት መብት አላቸው። ተፈጻሚ ከተደረገ ይህ መረጃ የደንበኛውን መረጃ ምድቦች እና ከዚህ የካላንደር አመት በፊት የደንበኛውን መረጃ የገለጽንላቸው የንግድ ድርጅቶችን ስሞችና አድራሻዎች ሊይዝ ይችላል።
© 2004-2023 Young Life. All rights reserved.